መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በጸሎቱ በንቃት እየደገፈው እና እንደአይኑ ብሌን እየጠበቀው የሚገኘውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ እስከ አሁን ድረስ ከ 200 ሺ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የጎበኙት መሆኑም ይታወቃል EE ይህም ለሃገራችን ህዝብና ገንቢዎቹ ከፍተኛ መነሳሳትና መነቃቃት ከፈጠሩ ምክንያቶች መሃል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን ይልቁንም ግንባታው ያለአንዳች መወላፈት በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ አብሳሪ ነውEE በግንባታው ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት የተጣለባቸውን አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ሽንጣቸውን ገትረው ሌት ተቀን በመትጋት ላይ ስለመሆናቸው ለእይታ ክፍት የሆነውን የግንባታ ስፍራ በመጎብኘት ማረጋገጥ ይቻላልEE አሁን ልዩነቱ እና የዚህ ተረክ መነሻ በግድቡ ግንባታ ላይ ቅሬታና የተበሻቀጠ አቋም ይዘው ከነበሩ ሃይሎች መካከል ዋና የሆነችው ሃገረ ግብጽ ወደትክክሉ መስመር ስለመመለሷ በመሪዎቿ በኩል እየተናገረች በሚዲያዎቿና በልሂቃኖቿ በኩል ከአሸባሪ ሃይሎች ጋር ተባባሪ ሆኗ ግንባታውን ለማሰናከል ስትቋምጥ መታየቱ ነው። እንደሚታወሰው ባሳለፍናቸው አምስት አመታቶች ሁሉ በግብፅ በኩል የተለያዩ ቅሬታዎችሲቀርቡ ተደምጠዋልEE የግድቡ መገንባት በግብፅ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር እና ይልቁንም ህልውናቸውን እንደሚፈታተን ጭምር በመግለጽ ተቃውሟቸውን በተደጋጋሚ ማሰማታቸውምይታወሳልEE ያም ሆኖ ግን እውነታው የዚህ ተቃራኒ መሆኑ በተጨባጭ መረጃዎች ቀርቧልEE ግድቡ የተፋሰሱን ግብጽን ይቅርና ሁሉንም የተፋሰስ ሃገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በባለሙያዎች ጥናት ተረጋግጧል፤ፍትሃዊ የአባይ ውሃ ክፍፍልን መሰረት ያደረገ ፕሮጀክት መሆኑም እንደዛውEEየግድቡ መገንባት በተፋሰሱ አገራት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ አለመኖሩን ኢትዮጵያ ስለተናገረችሳይሆን በጥናት የተረጋገጠ ጉዳይ ነውEE ይህም ጥናት የተከናወነው ኢትዮጵያን ጨምሮ ቅሬታ አለን ሲሉ በነበሩት ሀገራትም ጭምር መሆኑ ይታወቃል። በሶስቱ የተፋሰሱ አገራት ( ኢትዮጵያ፤ ግብፅና ሱዳን) ትብብር የተመራው ይህ የአዋጭነት ጥናት በነሱ ይሁንታ ከተመረጡና ከየአገራቱ የተውጣጡ ስድስት ባለሙያዎችናበሶስቱ አገራት በጋራ የተመረጡ አራት ዓለም ዓቀፍ ባለሙያዎችንም ያካተተ መሆኑ ይታወሳልEEበዚህም የኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የዲዛይን ስራ አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ የዲዛይን መመዘኛናመርሆዎች ላይ የተመሰረተ፤ ለሶስቱም አገራት ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ፤ እንዲሁም በሁለቱ ተጋሪ አገራት(ግብፅና ሱዳን) ላይ ጉልህ ጉዳት የማያደርስ መሆኑን ቡድኑ በጥናቱ አረጋግጧልEE 1
ይህ ብቻ አይደለም በተፋሰሱ አገራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የማያስከትል፤ በአንፃሩ ልማትን የሚያፋጥን ታላቅፕሮጀክት መሆኑም ተመልክቷልEE ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማመንጨት የኃይል ፍላጎትን ለማሟላትየጀመረችው ጤናማ አካሄድ አንዱ አካል መሆኑንም ጭምር ያረጋገጠ ጥናት ነውEE የዓለማችን ትልቅ ስጋትእየሆነ የመጣውን የአየር ብክለትን ለመዋጋት አገሪቷ እየሄደችበት ያለውን የአረንጓዴ ልማት ስኬትም ያረጋገጠ ነውEE የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ግብ ኢትዮጵያ ከታዳሽ ኃይል የኤልክትሪክ ኃይልንበማመንጨት የዜጎቿን ፍላጎት ለማሟላትና ኢኮኖሚውን የሚሸከም ኃይል ማቅረብን የተመለከተው ዋነኛ ነው ። ከዚህም ባሻገር እነዚህ እና ግንባታው ይጎዳናል የሚሉ ሃገራት በተለይም ግብጽ የኤሌክትሪክ ኃይል በቀላሉየሚያገኙበት ዕድል የሚፈጥር መሆኑም ሌላኛው እና ከዋነኛው የማይተናነስ ግብ ነው EE በተለይም የተፋሰሱየታችኛው አገራት የሆኑትን ሱዳንና ግብፅ ከጎርፍ ስጋትና ከደለል ሙሌት ይታደጋቸዋልEE የውሃውን ትነትመጠን በመቀነስ ረገድም ድርሻው ጉልህ ነውEE ስለሆነም ግድቡ የተፋሰስ ሃገራቱ ሁሉ የጋራ ሃብት ነው። ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በተሳካ ሁኔታና የተፋሰስ ሃገራቱን የላቀ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ በሚያረጋግጥ የግንባታ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም የሙርሲው ካቢኔ እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ካስቀመጧቸው የማሠናከያ ስልቶች ውስጥ ኢትዮጵያን ማተራመስ፤ ለዚህ ደግሞ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን መጠቀም የሚለው ግንባር ቀደሙና እና በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የተቀመጠ ስትራቴጂ መሆኑ አይዘነጋም። ግብጽ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለማሰናከል ከዘረጋቻቸው ሥትራቴጂዎች መካከል ተቃዋሚውንና የጎረቤት ሃገራትን በተላላኪነት እና በአፍራሽ ተልዕኮ ማሣተፍ ነው የሚሉትን ሁለት አማራጮች በሙርሲ የተተካው የአልሲሲ መንግስት እንደማያደርገው ቃል ከመግባት አልፎ ለድርድር በሩን ከፍቶ የነበረ መሆኑ በብዙ የድርድር ማሳያዎች ተረጋግጦ የነበረ ቢሆንም ወደሙርሲ አቋም የተመለሱ ስለመሆናቸው የሚያጠይቁ አደገኛ አዝማሚያዎች ሰሞኑን በመታየት ላይናቸው። በአልሲሲ በሚመራው መንግስት ባለቤትነት ስር በሚገኘው አንድ የግብጽ ቴሌቪዥን የካላም ጁራይድ ወይም እንደኛው የሚዲያ ዳሰሳ አይነት ፕሮግራም አላቸው። የባለፈው ሳምንት የዚህ ፕሮግራም አጀንዳ በእርግጥም አልሲሲም እንደ ሙርሲ መሆኑን ያመላከተ መሆኑ ነው የዚህ ጽሁፍ መነሻና መድረሻ። አዘጋጁ ፕሮግራሙን ግና ሲጀምር አስደሳችና የግብጻውያንን ጉሮሮ የሚያርስና ልባቸውን በሃሴት የሚሞላ ዜና የደረሰው መሆኑን በመግለጽ ይገልጻል። ይህም ዜና ወደታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሚያመሩ መንገዶች ሁሉ መዘጋታቸውን የተመለከተ መሆኑን ያብራራል። ለዚህም ዜናው ምንጭ ያደረጋቸውን የኮንጎ2
ወንዝ አስተባባሪ ዶክተር ናንሲ ኡመር በቀጥታ ስልክ ያስገባው የካላም ጁራይድ አዘጋጅ ዶክተሯ ከኦሮሞ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ መሪዎች ጋር ቁጭ ብለው የተደወለላቸው መሆኑን በመግለጽ እነዚህ ተቃዋሚዎች በሰሞኑ አመጽ የግብጽን ባንዲራ እንዳውለበለቡ እና መንገዶችን ሁሉ ስለመዝጋታቸው አውስተው፤ መላው የግብጽ ህዝብ እና መንግስት ይህን አመጽ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል። የኦሮሞ ህዝብን የኩሽ ነገድ እንደሆነ እና የግብጽ አካል መሆኑን እስከመግለጽ የደረሱት ጋዜጠኛ እና ዶክተር ናንሲ የሃገራቸው የደህንነት ተቋም ይህን ስራ በአግባቡ እየሰራ መሆኑን አድንቀው ለነዚህ የጥፋት ሃይሎች የበለጠ ድጋፉን በማድረግ ኢትዮጵያን የማተራመሱን ስራ የበለጠ እንዲያጠናክርም ማሳሰባቸውን በአረብኛ የተላለፈው ዘገባ ያረጋግጣል። በዚህ ያላበቁት ዶክተር ናንሲ እና አዘጋጁ ዶክተር ፋዮም የተባሉ የሃገራቸው ምሁር እና በአባይ ላይ በተለየ እና ጽንፍ በረገጠ አቋሙ የሚታወቀውን ናስር በማስታወስ እና አባይን በተመለከተ ከተናገሯቸው እኛ እድሜ ልካችንን አናርፍም በየመንገዳችን ከቆመው ጋር ሁሉ እንቀላቀላለን የሚለውን እና ለመሞቱማ እዚያው ሄደን እንሞታለን የሚለውን በመጥቀስ ይልቁንም ፕሬዝዳንት አልሲሲ እነሱ የማደግ መብት እንዳላቸው ሁሉ እኛም የመኖር መብት አለን ማለታቸውን በማጉላትና ስንቅ በማድረግ የግብጽ ህዝብ እንዳይተኛ እና ተቃውሞውን በመደገፍ ግንባታውን ማሰናከል የሚገባው መሆኑንም አሳስበዋል ። የኦሮሞ ህዝብ ሺህ ጊዜ ቢከፋው የግብጽን ባንዲራ ያውለበልባል ማለት ሙልጭ ያለ ስህተት መሆኑ ቢታወቅም ማሳሰቢያቸውን ግን ከእሬቻ በአል የጥፋት አጀንዳ በስተጀርባ ሆነው የተናገሩትን ተግባር ላይ ማዋላቸው በተለያዩና ተጨባጭ በሆኑ አስረጂዎች ተረጋግጧል። ከላይ ለመጠቃቀስ የሞከርነውና በግብጽ ቴሌዥን አለም የተመለከተው አጀንዳ የኦሮሞን ህዝብ የማይወክል መሆኑ ቢታወቅም ግብጽ ኢትዮጵያ ለዘላለም ከርስ በርስ ጦርነት እንዳትላቀቅ ከኦነግ ጋር ጋብቻ ስለመፈጸሟ ግን የማያጠራጥሩና የማያከራክሩ አስረጂዎች በካይሮ እና በቢሾፍቱ ታይተዋልEE የካላም ጁራይድ ፕሮግራም አዘጋጅና ዶክተር ናንሲ ኡመር ባቀረቡት ጥሪ አግባብ በቢሾፍቱ ከትመው የከረሙት ተላላኪ ሃይሎች ያውለበለቧቸውን የኦነግ ባንዲራዎች፤ ያሰሟቸውን መፈክሮች እና የያዟቸውን ባነሮች፤ በካይሮ ለኦነግ አባሎች የአልሲሲ መንግስት ባዘጋጀው መድረክ የአልሲሲ ተወካዮች እና የኦነግ አባሎች አውለብልበውታል፤ ለብሰውትም ታይተዋል። የኦሮሞ ህዝብ ልክ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የራሱ የሆነ ቅሬታ ያለበት፣ ያስተዳደር በደል የደረሰበት ወዘተ መሆኑ ይታወቃል። ያም ሆኖ ግን ንብረቶችን በማቃጠልና የኦነግን ባንዲራ በሚያውለበልቡ ሃይሎች ቀሬታዬ ይፈታል በማለት የጥፋት ሃይሎቹን መታገሱ በተዘዋዋሪ ለግብጽ እጅ መስጠትና ላቡን3
እያንጠፈጠፈ የሚገኝለትን ታላቁን የኢትዮጽያ የህዳሴ ግድብ አሳልፎ እንደመስጠት መሆኑን ሊገነዘብይገባል። በመሰረቱ የእሬቻ በአል የፖለቲካ መድረክ ባይሆንም እና ፍትሃዊ የሆነ ጥያቄ እንኳ ቢኖር እዚያ ማንጸባረቅ ባይገባም ከዚያም አልፎ የነግብጽ አጀንዳ ማራገፊያ መሆን ውርደትና የሚያስቆጭ መሆኑንም መላው እና ሰላማዊ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ሊገነዘብና ድርጊቱን በይፋ ሊያወግዝ ይገባል። መንግስትም ከዚህ በላይ የግብጽን ድብቅ ሴራ አመላካች አያገኝምና ከዚህ ውጪ የሚያደርጋቸው የሁለትዮሽ ድርድሮች ላይ የቅኝት ለውጥ ሊያደርግ ተጨባጩ ሁኔታ ግድ ይለዋል። ከላይ ከተመለከቱት እና ማንም ተሸናፊ ከማይሆንባቸው ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ባሻገር በጥናትም የተረጋገጡ ውጤቶችን የሚገፉ ሃይሎችን መግፋት የሞራልም ሆነ የህግ ተጠያቂ አያደርግም። መላው ህዝብ ግን ለተራ አሉባልታ ሳይበገር እንቁ የሆነውን ፕሮጀክቱን በንቃት ሊጠብቀውና ከአፍራሽ ሃይሎች ፕሮፖጋንዳ ራሱን ሊከላከል የሚገባው ከሆነ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ስለመሆኑ ከላይ ከተመለከቱት አስረጂዎች በላይ ማረጋገጫ መጠበቅየለበትም። የጥፋት ሃይሎቹን እና ተላላኪዎቹን በመነጠል ኦሮሚያና ግብጽም ሆኑ ቢሾፍቱና ካይሮ ማንም ተሸናፊ ስለማይሆንበት ግንኙነት እንጂ ካይሮና ሃገረ ግብጽ የበላይ ለሚሆኑበት ግንኙነት እጅ እንደማይሰጡ መላው ህብረተሰብ ይልቁንም እወክልሀለሁ የሚለው የኦሮሞ ህብረተሰብ በይፋ ሊያረጋግጡ ይገባል።4