ኦነግና  ጀዋር

                                                                                       
 በኦሮሚያ በተፈጠረው ትርምስ ውስጥ እሳቱን ከመለኮስ ጀምሮ ጥፋትና ውድመቱን እስከ መምራትና ማስተባበር ድረስ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን በህዝብ ንብረት መውደምና በዜጎች ሕይወት መቀጠፍ ውስጥ በጀዋር ሚመራው የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክና ማህበራዊ ሚዲያው ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ ጀዋር መሀመድ በሁለት ካርድ ነው የሚጫወተው፡፡ በእስላማዊ አክራሪነትና ሌላም ከኦነግ ጋር በፈጠረው ሽርክና፡፡
ጀዋር ሲለው ኦሮሚያን ነጻ ማውጣት በሚል የኦሮሞ ብሄርተኛነትን ይሰብካል፤ በሌላው መድረክ ደግሞ ኦሮሚያ የሙስሊም ኦሮሞዎች ብቻ ናት ሲል ይሰማል፡፡ ጀዋር “እኛን የሚቃወም አንገቱን በሜንጫ (ገጀራ) እንቀላዋለን” የሚልና ጭፍን አክራሪ እስላማዊነትን የሚያራምድ ፅንፈኛ ሲሆን ይህን ተግባሩን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎችም አሉ፡፡
ጀዋር መሀመድ ዘረኛና ይባስ ብሎም አክራሪና አሸባሪ ሙስሊም ነው፡፡ በጀዋር ግልጽ አባባል ክርስትያንና የሌላውም እምነት ተከታይ የሆኑ ኦሮሞዎች እሱ በሚያስባት ኦሮሚያ ውስጥ ቦታ የላቸውም፡፡ ይሄ የተዛባና ከህዝብ እምነት ያፈነገጠ የጀዋር መሀመድ ጥልቅና አውዳሚ እምነትና አስተሳሰብ የት ድረስ ሊወስደው እንደሚችል ለመገመት አይከብድም፡፡ ጀዋር ልክ እንደ ኦነግ ሁሉ ተቀባይነት የሌለው፣ የህዝብን አብሮነት የሚንድ፣ የከፋ የእርስ በእርስና ሀይማኖታዊ ግጭት ሊያስነሳ የሚችል፣ መርዘኛ፣ ሀገር አጥፊና ለህዝብም ሰላም አደገኛ የሆነ አካሄድን የሚከተለው ፀረኢትዮጵያ አቋምን የሚያራምድ (ፖለቲከኛ ሳይሆን) ግልብ ሰው ነው፡፡ በዚህ ባለንበት በሰለጠነና የህዝቦች አብሮነት በሚሰበክበት ዘመን እንደዚህ እንደጀዋር ለማሰብ ይከብዳል፡፡ ሰው ሆኖ የተፈጠረ ሰው በሀገሩ፣ በህዝቡና በድሀ ወገኑ ሞት፣ በሰላም ማጣት፣ በንብረት መውደም ወዘተ ደስተኛ ይሆናል ብሎ ለማሰብ በእጅጉ ይከብዳል፡፡
ጀዋር መሀመድ ጽንፈኛ አክራሪ እስላማዊ እምነትን በመላው ኦሮሚያ ለማስረጽ ግዜ ወሰዶ መዋቅሩንም በወኪሎቹ አማካኝነት ለማስፋፋት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ዛሬ ላይ በተግባር የታየ እውነት ነው፡፡ የኦነግ አመራር ቀደም ባሉ ሩቅ ግዜያት በውስጡ ተደጋጋሚ መከፋፈል ተከስቶበት የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አክራሪ እስላማዊ ክንፉ ተገንጥሎ የራሱን እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበረ ይታወቃል፡፡
በተለይም በሀረር፣ በጅማ፣ በባሌ፣ በሰሜን፣ ሸዋ ከሚሴ፤ በቤኒሻንጉል ጉምዝ አካባቢም የታዩት የአክራሪ እስላማዊ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ መንግስት ሲናገር ለራሱ የፖለቲካ ፍጆታ ሲል ነው እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም አይነት የእስላማዊ አክራሪ እንቅስቃሴ የለም በማለት ሲያጣጥሉ የነበሩት የሀገር ውስጥና የውጭ ጽንፈኛ ተቃዋሚዎች የችግሩ ግዝፈት ምንያህል እንደተራመደ በተጨባጭ ምልክቶቹን እያዩ በመሆናቸው ሊክዱት አይችሉም፡፡  
ኢህአዴግን መቃወም መብታቸው ቢሆንም በከፋ ደረጃ ሀገሪቱን ለማጥፋት አድብቶ ሲንቀሳቀስ የቆየውና በግብጹ ሙስሊም ብራዘር ሁድ በመመራት መሰረቱን ኢትዮጵያ ወስጥ የጣለው አክራሪ እስላማዊ ቡድን በኦሮሚያ አካባቢ ከተከሰቱ የሀገርና የህዝብ ሀብት የማቃጠልና የማውደም ድርጊት ጀርባ ዋነኞቹ ተዋናዮች የነጀዋር መሀመድ የነኦነግ የነግብጽ ትእዛዝ መመሪያና እጅ  ነው፡፡
ጀዋር መሀመድ በግብጽና በሌሎችም የዋሀቢና የሰለፊያ አክራሪ እስላማዊ እምነት ቀንደኛ አራማጅ በሆኑና ኩዌት ኳታር ሳኡዲ አረቢያን በመሰሉ ሀገራት ጭምር እንደሚረዳ ጥርጥር የለውም፡፡ በአሜሪካን ያቋቋመው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ግቡ ያደረገው በኦሮሚያ ያሉ ሙስሊሞች ነጻ ወጥተው የራሳቸውን እስላሚያ ኦሮሚያ መንግስት መመስረት አለባቸው የሚል ነው፡፡ የግንቦት ሰባት ልሳን የሆነው ኢሳት ሳተላይት ቴሌቪዝንም የሚረዳው በግብጽና በእነዚሁ መንግስታት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአንድ ወቅት ከግብፅ መንግስት 500ሺ ዶላር በሻእቢያ መንግስት በኩል እንደደረሰው ተጨባጭ ማስረጃዎች ያሉ ሲሆን ሊ/መንበሩም ይህንኑ በአደባባይ፣ ትንሽ እንኳን ሳያፍሩ ተናግሮታል፡፡
ቀደም ሲል እንደተናገርነው፣ ጀዋር በሁለት ካርታ የሚጫወት ግለሰብ ሲሆን የመጀመሪያው ፍጹም አክራሪ እስላማዊ እምነት አራማጅና ይሄንኑም በስፋት ወደ ኢትዮጵያ ለማስረጽ መዋቅሮቹን ሲዘረጋ ሁከት፣ አመጽ፣ ረብሻ እንዲቀሰቀስ ሌት ተቀን ሲሰራና ሲያስተባብር፣ በተግባርም በተለያዩ አካባቢዎች እንደታየው ንብረት የማቃጠልና የማውደም ስራዎችን በሶሻል ሚዲያውና በራሱም ሚዲያ አማካኝነት ሲመራ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሌላው ከኦነግና ከግብጽ ጋር ያለውን ግንኙነት በኦሮሚያ የተከሰተውን አመጽ ለማስፋት ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆን ረዥም ርቀት በመሄድ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በቅርቡ ኦነግ በኦሮሚያ በአጠቃላይ የተደረገውን አመጽና ንቅናቄ የመራሁት እኔ ነኝ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ ሲል መግለጫ አውጥቶአል፡፡
ከሰሞኑ አንድ ይፋ የሆነ ማስረጃ ኦነግ የግብጽን መንግስት 2.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቁን ይፋ አድርጓል፡፡ ኦነግ ይህንን ገንዘብ ከግብጽ መንግስት የጠየቀው በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በኦሮሚያ ሁከት፣ ትርምስና አመጽ እንዲስፋፋ ለማድረግ ምናልባትም መሳሪያዎችን ለመግዛት እንዲሁም ለጥፋት ተልእኮው ለሚያሰማራው ቡድን ከፍተኛ የመደለያ ክፍያ ለመክፈል ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡
ይሄ የቅርብ ማስረጃ በመገኘቱ እንጂ ቀደም ባሉት ግዜያት ከፍተኛ መጠን ያለው የግብጽና የሌሎችም አክራሪ እስላማዊ መንግስታት ገንዘብ በተለያየ ምስጢራዊ መልኩ ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ እንዲሰራጭ ስለመደረጉ ጭምጭምታዎች አሉ፡፡ ይህ ሁሉ እችን አገር ለማጥፋት ሲባል እየተደረገ ያለ እኩይ ተግባር ነው።
ይህን ገንዘብ ወደዚህ የሚያስገቡበት ዋና አላማ ለኛ ድልድይ ሊሰሩልን አየደለም፤ ገንዘቡን ሊያውሉት የሚችሉት አንድም በተለያዩ የእነሱ አጋር በሆኑ ኢንቨስተሮች አማካኝነት ወይንም ግብጽን በመሰሉ ኤምባሲዎች ባሉ፣ ለዚሁ ተግባር በተመደቡ የደህንነት ሰዎቻቸው አማካኝንት የተለያየ ሽፋንን በመጠቀም በአዲስ አበባና በክልሎች ለሚገኙት እነሱ ብቻ በምስጢር ለሚያውቁአቸው  አባሎቻቸውና ወኪሎቻቸው ማከፋፈል ነው፡፡    
ከእነዚህ ኤምባሲዎችና ከሌሎችም ወዳጆቻቸው ጋር የተያያዙ፣ በኢትዮጵያ የተከፈቱ፣ በእነሱ ሰዎች የሚመሩ፣ የልማትና የቴክኒክ ትብብር የተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ፋብሪካ እርሻ በማስተማር ላይ ያሉ ቋሚ ንግድ ቢሮ የከፈቱ አዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ በአማራ ክልል በሚኖሩ በሚንቀሳቀሱት ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ መንግስት አያውቅም አይባልም፡፡
ሌሎችም ኢትዮጵያ ውሰጥ በተለያየ ምክንያትና ሽፋን ገብተው የሚሰሩት ሀገራችንን ለመሰለል ለሀገራቸው መረጃ ለማቀበል ተባባሪዎቻቸው በሆኑትና በገንዘብ በገዙዋቸው የራሳችን ዜጎች አማካኝነት በሀገሪቱ ውስጥ ሁከት፣ ብጥብጥ፣ አመጽ እንዲቀሰቀስ፤ ትርምስ እንዲፈጠር፤ ቀውሱ በተለያዩ አካባቢዎች እንዲስፋፋ፤ የእለት ከእለት የህዝቡ ሰላማዊ ህይወት እንዲናጋ ፤ትራንስፖርት ከቦታ ቦታ እንዲቋረጥ፤ የንግድ ልውውጡና ግብይቱ እንዲቆም፤ መሰረታዊ ተፈላጊ ሸቀጦች እያሉም ከገበያ እንዲጠፉ ህብረተሰቡ እንዲማረር ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማድረግና የመሳሰሉትን የውጭ ሀይሎችና የውስጥ ተባባሪዎቻቸው ተቀናጅተው በህዝቡ ውስጥ የሚፈጽሙት ወንጀል ነው፡፡ ይሄም በሚገባ ይታወቃል፡፡
መንግስትን ውጥረት ውስጥ መክተት፤ ሀሳቡም ሀይሉም እንዲበታተን ማድረግና ሌሎችም በሀገራችን ውስጥ ሲሰሩ የቆዩት በግብጽ ደህንነት ሰዎች፣ በነኦነግና በነጀዋር መሀመድ ቡድኖች መሆኑ ዛሬ ከምንግዜውም በላይ ይፋ ወጥቶአል፡፡ የጸረኢትዮጵያ ሀይሎች ሀገር አፍራሽ ሴራ ተባባሪ በመሆን ሀገራችንን ለመበታተን ለረዥም ግዜ አድብተው ሲሰሩት በቆዩት ስራ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች በንግድና በኢንቨስትመንት በተለያዩ ዘርፎች ትራንስፖርት፣ ሆቴሎች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ በጅምላ አከፋፋይነት፣ በሱቆች ወዘተ ሰፊ ካፒታል ተመድቦላቸው በሽፋን ሲሰሩ የኖሩና ያሉ የጠላት ተላላኪ የሆኑ ዜጎች በብዛት እንደሚኖሩ ይታመናል፡፡ ካለውስጥ ተባባሪ ሀይሎች ኦነግም ሆነ ጀዋር መሀመድ  ወይንም ግብጾች የፈለጉትን ያህል ርቀት መሄድ እንደማይችሉ ይታወቃል፡፡ ይህም የሚያሳያው የሴራው መረብ መበጠስ ያለበት ከውስጥ ሊሆን የሚገባ መሆኑን ነው፡፡ በዚህም፣ የኦነግና የጀዋር መሀመድ ሀገር የማጥፋት ተልእኮ በመንግስትና በህዝቡ ታላቅ ርብርብ  ይመክናል፡፡