መርህ የለሽነት እንደ መሰረታዊ ችግር

እንደ አንዳንድ የፍልስፍናው ዓለም ሊቃውንቶች አስተምህሮ፣ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የህይወት መመሪያ (መርሆ) ይኖረው ዘንድ ግድ ነው፡፡ ለዚህ ዓለም አቀፍ የፍልስፍና እሳቤ እንደመነሻ የሚወሰደውም ደግሞ ግሪካዊው ፈላስፋ ሶቅራጥስ ነው፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደኖረ የሚነገርለትና ለዛሬው ዘመን ስልጡን ዓለም ጭምር የፍልስፍናዊ አስተምህሮ አባት ተደርጎ የሚቆጠረው የጥንታዊቷ ግሪክ ዜጋ ሶቅራጥስ፤ ለሰው ልጆች ይበጃል ብሎ ያመነበትን አስተሳሰብ ለማስረፅ ያለመ ትምህርት ይሰጥ እንደነበር ይታወቃል፡፡ እናም የኋላ ኋላ ነገረ-ስራውን ባልወደዱለት የአቴና ገዥዎች ተወንጅሎ በመከሰሱ ምክንያትየሞት ፍርድ ተበየነበት፡፡ ይህንን የሰሙ የሶቅራጥስ ደቀመዛሙራትለታሰረበት ወህኒ ቤት ጠባቂዎች ጉቦ ከፍለው ሊያስመልጡት ሞክረው እንደነበርም ተደጋግሞ ይወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ሶቅራጥስ የደቀመዛሙራቱን ጥያቄ በመቃወም “እንደምታውቁት እኔ እስከ ዛሬ ድረስ የኖርኩት፤ ለሰው ልጆች ሁሉ ፍትህና ርትዕ እንደሚያስፈልጋቸው በማስተማር ነው፤ ታዲያ እንዴት አሁን ጉዳዩ እኔን ራሴን በቀጥታ የሚመለከተኝ ሆኖ ሲገኝ ፍትህን በጉቦ ገድላችሁ ህይወቴን እንድታተርፉልኝ እስማማለሁ?ፈፅሞ አላደርገውም!” ሲል እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይህ እያንዳንዳችን በምክንያታዊነት ላይ ተመስርተን የገሃዱን ዓለም ተጨባጭ እውነታ እየመረመርን ለመረዳትና ለሰው ልጅ ህልውና መቀጠል የሚበጀውን ከማይበጀው (ጎጂውንከጠቃሚው) መለየት እንድንችል፤ የህይወት መስዋዕትነትን እስከ መክፈል የሚደርስ ቁርጠኛ አቋም መያዝን የሚጠይቅ፤ የጋራ አሊያም የተናጠል መርሆ ሊኖረን እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ነው ፡፡

ከላይ የቀረበው መንደሪደሪያወደ ዋናጉዳይ የሚወሰደን ሲሆንየፅሁፉትኩረት  በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች እንቅስቃሴ ውስጥ መርህ የለሽነት እንደ መሰረታዊ ችግር የሚገለፅበትን  ሁኔታ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡

አብዱራህማን አህመዲን የተባሉ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፓርላማ አባል፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት “ሰንደቅ” ጋዜጣ ላይ “የዶክተር ኃይሉ አርአያና የአቶ ታምራት ታረቀኝ መርህ አልባነት” በሚል ርዕስ እኔ ዛሬ ካነሳሁት ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያለው መጣጥፍ አቅርበው እንደነበር ማስታወስ ተገቢ መስሎ ይሰማኛል፡፡ ስለሆነም አቶ አብዱራህማን በፅሁፋቸው ርዕስ ስማቸው የተጠቀሰውን ሁለት የተቃውሞው ጎራ ፖለቲከኞች መነሻ አድርገው “የኔ ሃሳብ” በሚለው የሰንደቅ ጋዜጣ አምድ ስር ያስነበቡን ትችት አዘል መጣጥፍ ላይ “… ምንም እንኳን ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከዚህ ዓይነቱ የመርህ አልባነት ችግር ነፃ ነው የሚል እምነት ባይረኝም የችግሩ ስፋትና ጥልቀት ጎልቶ የሚስተዋለው በተቃዋሚው ጎራ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ስለመሆኑ ግን ደፍሮ መናገር ይቻላል” ሲሉ የኢ.ዴ.ፓ. አመራር አካል በነበሩበት ወቅት ካጋጠማቸው ተጨባጭ እውነታ ጋር እያጣቀሱ ያቀረቡትን ሃሳብ እኔም እንደምጋራው በዚህ አጋጣሚ ልገልፅላቸው እወዳለሁ፡፡

ምክንያቱም የኢትዮጵያን የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከትናንት እስከ ዛሬ ክፉኛ የሚያምሰው ከአባላቱ (በይበልጥም ደግሞ ከአመራር አካላት) ስር የሰደደ መርህ የለሽነት የሚመነጭ ውስጣዊ ችግር እንደሆነ አቶ አብዱራህማን አስምረውበታልናነው፡፡ ፀሐፊው ‹‹ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከዚህ ዓይነቱ የመርህ አልባነት ችግር ነፃ ነው የሚል እምነት ባይኖረኝም›› ሲሉ እግረ መንገዳቸውን የሰነዘሩት አስተያየትም ቢሆን፤ ልብ ሊባል የሚገባውን ቁም ነገር ያዘለ እንጂ ለይስሙላ የቀረበ ንፅፅር አልነበረም ባይ ነኝ እኔ፡፡

የአቶ አብዱራህማን አህመዲን መጣጥፍ አጠቃላይ ይዘት፤ በተለይም የዶክተር ሃይሉ አርአያንና የአቶ ታምራት ታረቀኝን ከኢ.ዴ.ፓ. አባልነት ወደ የቀድሞው ቅንጅት፤ እንዲሁም ደግሞ ከቀድሞው ቅንጅት ወደ አንድነት ፓርቲና ከዚያም ወደ የዛሬው ሰማያዊ እያለ የቀጠለ የስልጣን ሽኩቻ የወለደው ፖለቲካዊ አክሮባት ከውስጥ አዋቂ ትዝብታቸው በመነጨ ማጣቀሻ  አስደግፈው የተቹበት ምክንያታዊ ትንተና ሚዛን ደፍቶ ማግኘቴን አስታውሳለሁ፡፡ ትችታቸው ከደርግ ውድቀት ማግስት ጀምሮ በምናውቀው የሀገራችን የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደ ባህል የተወሰደ እስኪመስል ድረስ ሲደጋገም የሚስተዋለውን፤ ጎራ ላይቶ የመቧደንና የፓርቲ አመራር ስልጣንን የመጨበጥ ፍላጎት በሚፈጥረው የውስጥ ሽኩቻ ምክንያት እርስ በርስ እየተጠላለፉ ለመውደቅ አደጋ ሲዳረጉም ጭምር የታዘብንበትን ክስተት የሚያጠቃልል ገፅታ እንደነበረው አሁንም ጋዜጣውን  በማየት ማረጋገጥ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ለነገሩ በዚህ ረገድ ስለሚስተዋለው አሳሳቢ ችግር ሌሎች ሊቃውንትም ጭምር በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ማድመጥ የተለመደ ጉዳይ እንደሆነ ደፍሮ መናገር ይቻላል፡፡ በተለይም ደግሞ የፅንፈኝነት አባዜ የተጠናወተውን የትምክህት እና የጠባብ ብሔርተኝነት አስተሳሰብ ጎራ ወክለው የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች በአጠቃላይ የሀገራችን ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የሚያቀነቅኑት ቡድኖች መርህ የለሽነትን እንደ ባህል እየቆጠሩት ስለመምጣታቸው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚሰጡትን ማሳሰቢያ ማስታወስ ይቻላል፡፡ 

    እንዲያውም እውነቱን መነጋገር ካለብንማ፤ በተለይም አሁን አሁን ኢህአዴግ መራሹን የኢትዮጵያውያን ህዝቦች የትግል መስመር ወዳልተለመደ የአመለካከት ብዥታ የመሔድ አዝማሚያ  እንዲታይበት ሲያደርጉ