መልዕክት ከዲያስፖራው ለዲያስፖራው

ሰው በተለየዩ ምክንየቶች እናት ሀገሩን በመልቀቅ አንድም ቀን የማያውቀውን ቢነገረውም በማይደንቀው የስደት ሀገር ወዶም ይሁን ተገድዶ ሲኖር ይታያል፡፡ ይህ መለት ግን አምጣ የወለደችውን፣ እትብቱን አትባ በአፈርዋ የቀበረችዋን እናት ሀገሩን በድህነት አለንጋ ስትገረፍ የሚጨክን አንጀት ይኖረወል ብሎ መገምት የማይታሰብ ነው፡፡ ይልቁንም አምጣ የወለደችው፣ ተርባ የጎረሰችው የእናት ሀገሩ ልጆች ከርሀብ ወጥተው ጠግበው ሲበሉ፣ ከእርዛት ወጥተው ሲዘንጡ እንደመየት ምን ደስታ አለ?

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከረጂም ጊዜ በፊት ጀምሮ ሳትወድ በግዷ የጎተራዋ ቀስ በቀስ መሳሳትና በውስጧ በተፈጠሩ የልጆቿ የዕርስ በርስ አለመግባባት የመህፀኗን ፍሬዎች እንባ እየተናነቃት አሰልፋ ለባዳ ሀገራት ሰጥታ በትካዜና በሲቃ ፊትዋ ተሸብሽቦ እና የወለደ አንጀቷ ቆስሎ ቆይታልች፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ላይነጋ አይጨልምም እንደሚባለው እንባዋን የሚያብስ፣ አንጀቷን የሚያርስ እና አንቺ ቀና ብለሽ እኔ አንገቴን ልድፋ የሚል የበኩር ልጅ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ካገኘች ሰነባበተች፡፡

ይህም ልጇ ትናንት በጠላትነትና እርስ በእርስ በደም ሚፈላለጉትን ልጆቿን በፍቅር አስደምሮ፣ እንደ መዥገር የናታቸውን ደም ሲመጡ የነበሩ ልጆቿም ይቅር ባይነትን አስተምሮ፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ጥፋት አጥፍተው የሰሩትን ምህረት ሰጥቶ፣ እድሜያቸውን ሙሉ ሀገራቸውን በማገልገል የነበሩትን ታላላቅ ልጆቿን እስኪ እረፉ ብሎ በጡረታ አሰናብቶ ለእናት ሀገሩ የተሻለ መፀዒ-ዕድል ሃያ አረት ሰዓትና ሰባት ቀን እየተጋ ይገኛል፡፡

ታድያ ትላንት ወደውም ይሁን ተገደው ከእናት ሀገራቸው ርቀን የነበርን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትጵያውያን ለዚህ የበኩር ልጇ ፈጥነን ታላቅ ወንደማችን ከጎንህ ነን ማለት ሰብዐዊነትና ለሀገር ተቆርቋሪነት ነው፡፡ ታላቅ ወንድማችን ጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ይፋ ካደረገውና ብዙ በድህነት የተጎሳቆሉ እህት ወንድሞቹን ከወደቁበት ለማንሳት ይረዳኛል ላለው ትረስት ፈንድ ከማኪያቷችን አንድ ዶላር ቀንሰን ገቢ ከማድረግ በሸጋር እናት ሀገራችን ኢትዮጵየን በተለየዩ መስኮች ልንረደ ይገበነል፡፡

እንደሚታወቀው እኛ ኢትዮጵያውያን አሁን ተሰደን በምንኖርባቸው የተለያዩ ሀገራት ኑሮን ለማሸነፍ ደከመን ሰለቸን ሳንል ብዙ ውጣ ውረድ አይተን ያፈራነው  ሀብትና ያካበትነው እውቀት አለ፡፡ ይህንንም ሀብትና እውቀታችንን ታላቅ ወንድማችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፈጠረልን አጋጣሚ ተጠቅመን እድሜያችንን ሙሉ የፈርነውን ሀብታችንንና እወቀታችንን ምንም ሳንሰስት ሀገራችንን አለንልሽ ልንላት ይገባል፡፡

በተጨመሪም በየሄድነበትና በየደረስንበት ሁሉ እናት ሀገራችን ያለት የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ፀጋዎች ለሚጠይቁን ወደጆችና ለሚንቁን ጠላቶች እኛ በፍቅርና በመደመር ስሜት ገልፀን ልናሳያቸው ይገባል፡፡ ደስ ሚለው እኛ ዲያስፖራዎች ከተማሪ እሰከ ተመራመሪ፣ ከእንጂነር እስከ ፕሮፌሰር እና ከፖለቲከኛ እስከ ጠፈርተኛ ችግር የሌለብን በመሆኑ አምጣ የወለደችንን ሀገር ከወንድማችን ተደምረን በመገኘት እናት ኢትዮጵያችን ወልዳ መካን እንዳልሆነች ልናሳይ ይገባል፡፡

በመሆኑም እውቀት ያለን በዕውቀታችን ገንዘብ ያለን በሃብታችን ሺህ ሆነን እንደ አንድ፣ አንድ ሆነን እንደ ሺህ በማሰብና በመተሳሰብ የእናታችንን አንገት ቀና ልናስደርግ ይገባል፡፡ ድሮም እኛ ኢትዮጵየውያን ወገን ሲያለቅስ አይደለም አይኑንም ሲዳብስ ምን ሆንክ ወደጄ የምንል ከእኔነት እኛነትን የምናስቀድም በመሆኑ ለወገኖቸችን ቀድመን አለንለችሁ ለወንድማችንም ጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ አህመድ ከጎንህ ነን  አናሳፍርህም ልንለው ይገባል፡፡ እንደሚታወቀው ታላቅ ወንድማችን በተለየዩ ጊዜያት ከእናት ቤታቸው የተበታተኑ እህትና ወንደሞቹን ለመሰብሰብ በሚኳትንበት ሰዓት እኛ ወንድሞቹ ደግሞ በእናት አገራቸው ላይ ተሰባስበው የእኛን የቴክኖሎጂ፣ የእውቀት እና የልምድ እርዳታ ለሚፈልጉ እህትና ወንድሞቻችን ቀድመንና ፈጥነን ልንደርስላቸው ይገባል፡፡

እናት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሱ እና ሀገራቸውን ወደ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚጋብዝ፣ የሚለምንና የሚማጸን ልዩ የሆኑ ወጣት ወንድምና መሪ አፍርታለች፡፡ ላለፉት አስራ ሦስት ዓመታት ገደማ ያህል ከኢትዮጵያ አቦሸማኔው ትውልድ መካከል አንድ ኢትዮጵያ እና የማትከፋፈል ሀገር በማለት የሚያውጅ እንደዚህ ያለ መሪ እንዲወጣ እና እንዲህ የሚለው የማንዴላ ቃል ኪዳን በኢትዮጵያ እውን ሆኖ እንድናይ ጠንካራ የሆነ ፍላጎችን እሙን ሁኖዋልና፡፡