ከለውጡ ፋይዳዎች …!

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ሁሉንም ወገን በበጎ አይን ሊመለከተውና ለስክታማነቱ የድርሻውን አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ለውጡ ካመጣቸው ዓበይት ስኬቶች አንዱ የአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸው ነው፡፡ መንግስት ይህንን እውን ለማድረግ ማለትም የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ከወሰዳቸው አወንታዊ እርምጃዎች መካከል በጥላቻ ይተያዩ የነበሩ ወገኖችን ማስታረቅ ነው፡፡

በዚህ መልክ በሃይማኖት መከፋፈል እንዲያበቃና በወጭና በአገር ውስጥ በሚል በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች መካከል ለሃያ ሰባት ዓመታት የነበረው መከፋፈልና ይህንን ተከትሎ ደግሞ በመእመናን ዘንደ ተፈጥሮ የነበረው ጥላቻ እንዲያከትም ማድረግ ተችሏል፡፡ ከዚህ ረገድ የተፈጠረው አንድነት ለአገር አንድነትና በአገራችን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን እውን ለማድረግ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ሙሁራን ይናገራሉ፡፡

አገር ውስጥም እስልምና ሃይማኖት መካከል ተነስቶ ነበረውን መከፋፈል ወደ አንድ እንዲመጡ ማድረግ መቻሉ ለአገሪቱ ሰላም የሚኖረው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም፡፡

ለከላይ የተገለጹት ሁለት ሃይማኖታዊ ጉዳች ፖለቲካዊ ትርጉምም አላቸው፡፡ በአንድ በኩል አማኞች መከፋፈል የአገሪቱኘ ህዝቦች መከፋፈል ማመጣቱ ስለማየቀር አማኞቹ መደመር ደግሞ ለአገሪቱ ህዝቦች መደመር ወሳኝ መሆኑ ነው፡፡

ሌላው ዓቢይ ተግባር ደግሞ ካሁን ቀደም በፖለቲካም ይሁን በሌላ ምክንት አገራቸውን ለቀው በተለያዩ የውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ፍራቻ ወደ አገራቸው ገብተው በአገራቸው ሁለንተናዊ ጉዳይ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየተደረገ ያለው ጥረት ነው፡፡

ሁሉም በውጭ የሚኖሩ የአገሪቱ ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተው ያለምንም መሸማቀቅ በአገራቸው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጉልህ ተሳትፎ ንነዲያደርጉ ለማድረግ መንግስት ተነሳሽነት ወስዶ በማንኛውም ደረጃ ይቅርታን በማስቀደም አገሪቱን ለመገንባት ሁሉም ተሳታፊ የሚሆንብት መላ መቄቀየሱ ምህዳሩ እንዲሰፋ አድርጎታል፡፡

መንግስት ያደረገውን ያላሳለሰ ጥረት ግምት ውስጥ በማስገባት በኩል መወሰዱንና ይህንን ተከትለው ወደ አገር ቤት የገቡ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች በተለያየ አጋጣሚ ለሚዲዎች እንደገለጹት መንግስት ለውጥ እያመጣ በመሆኑ የለውጡ አካል ለመሆን እንደሚሹና ለአገሪቱ ዴሞክራሲ መጠናከርና ዘላቂ ሰላም መስፈን አጋር ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡

ልላው ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ዓቢይ ጉዳይ ደግሞ የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት የዴሞክራሲ የደም ስር መሆኑን በመገንዘብ  አንድ ሰው ያመነበትን ሃሳብ በፈለገው መንገድ የመግለጽ፣ ተሰባስቦ የመቃወምና የመደገፍ፣ የመምረጥና መመረጥ፣ መንግሥትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገር እና ያለመናገር፣ የግል ኃይማኖትን መከተልና  የማስፋፋት መብቱ በተግባር እንዲረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት ነው፡፡

ይህንን  ማንም ሊገስሰው የማይችልመሠረታዊ ነፃነት ለዜጎች ለማጎናፀፍ ሲባል መንግሥት ሕገ መንግሥት በማርቀቅና የፕሬስ ሕግ በማውጣት ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትንም ሆነ የመረጃ ነፃነት ጉዳይን ዕውን ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን አከናውኗል፡፡

ይህንን ደንብና ህግን ወደ መሬት በማውረድና እንቅፋቶች ሲያጋጥሙ በህጉ መሰረት እየፈቱ የመሄድ ችግሮች የነበሩ ሲሆን አሁን የመጣው ለውጥ እነዚህን ችግሮች በተገቢው መንገድ ለመፍታት የሚያስችልና በህግ ደረጃ የነበረውን በተግባር ለመለወጥ የሚያስችል በመሆኑ ለውጡን ማገዝ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡

ምንም እንኳን ይዘታቸው በዳበረ መረጃ ላይ ከመመስረት ይልቅ ወሬና አሉባልታ ላይ የተመረኮዙ፣ ሚዛናዊነትና ገለልተኝነት የጎደላቸው፣ የግልና የቡድን የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ በመሆናቸው ውድቀታቸው ቢፋጠንም ከ1997 ዓ.ም በፊት ባሉት አሥርት ዓመታት ውስጥ በርካታ የጋዜጦችና የመጽሔት የኅትመት ውጤቶች ለንባብ ሲቀርቡ ነበር፡፡

በወቅቱ የነበረውን የፖለቲካ ትኩሳት መሰረት በማድረግ አንዳንዶቹ በመንግስት ሃላፊዎች በኩል በሚደረግባቸው ባልተጻፈ ህግ ላይ የተመሰረተ ጫና ሌሎቹ ደግሞ በጋዜጠኝነት ሙያ ክፍተት ምክንያት በህዝብ በኩል ተዓማኒነት በማጣታቸው የተነሳ ከጫወታ ውጭ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 ላይ የዜጎች ሐሳብን የመግለጽ፣ ያለገደብ የመናገርም ሆነ የመጻፍ መብት በመደንገጉ ከጋዜጣና ከመጽሔት በተጨማሪ በኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃን፣ በማኅበራዊ ድረ ገጽም ይሁን በኪነ ጥበብና በሥነ ጽሑፍ ሥራ ማዕቀብ ባለመጣሉ ለዴሞክራሲያዊ ባህል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 19 ከተጠቀሰው የሰው ልጅ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ዴሞክራሲያዊ እሴት አንፃር ሲታይ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው አካሄድ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ተግባራዊነቱ ላይ ግን ሙሉ ነው የሚባል አይደለም፡፡

                                                                 

ባለፉት 20 ዓመታት አብዛኞቹ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ሙያተኞች መረጃን በመከልከል ወይም ምስጢር በማድረግ ጉዳይ ላይ ተጠምደው በመክረማቸው አንዳንድ የመንግሥትም ይሁኑ የግል መገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊነት የጎደለው፤ ያልተጨበጠ የሀሰት ዘገባና አሉባልታ ለማሰራጨት የተገደዱበት ሁኔታ እንደነበር ማንም የሚክደው አይሆንም፡፡

በርካቶቹ መገናኛ ብዙኃኑ በደምሳሳው የሀሰት ዘገባ ያቀርባሉ ባይባልም አንዱ ከሌላው በተሻለ ደረጃ ላይ ከመሆናቸው ባሻገር በጥረት ለረጅም ጊዜ የዘለቁና ተዓማኒነትን ያተረፉት እንዳሉ ታይተዋል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ግን የጋዜጠኝነት ሙያና ተቋማቱ የሕዝቡን የዴሞክራሲ እሴቶች ማጎልበት የሚያስችልና የሚመጥን ደረጃ ላይ እንዳልነበሩ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

የፕሬስ ነፃነት ሃሳብን በኤሌክትሮኒክስ እና የህትመት መገናኛ ብዙኃንን ጨምሮ በማንኛውም መንገድ የመግለፅ መብት ማለት ሲሆን፤ ይህ መብት መረጃን ጠይቆ ማግኘትና ማሰራጨትን ያጠቃልላል።  ይህን መብት ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ውጪ ተግባራዊ የማድረግ ፍላጎት ቢኖርም ለተለያዩ ዓላማዎች ሲባል ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊ ጥበቃዎች ተደርገውለት የሚፈፀም ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በፓርላማ ከተሰየሙበት ጊዜ አንስቶ በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተዘዋወሩ ባደረጓቸው ንግግሮች የንግግር ነፃነት አስፈላጊነትን ሰብከዋል፤ ለንግግር ነፃነት ልዩ ቦታ ሰጥተዋል፤ በዚህም የእኔ ሐሳብ ብቻ ካላሸነፈ ሞቼ እገኛለሁና ከእኔ ሌላ አማራጭ የለም ባይነትን አስተንፍሰዋል:: የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግሮች ያዘሏቸው ቁም ነገሮች በሕገ መንግሥቱ የሠፈረውን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት የአንቀጽ 29 ፋይዳን ምንነት የሚያስረዱ ናቸው፡፡

የፕሬስ ነፃነትን ማክበር፣ መረጃን ማግኘትና ለሕዝብ ማሰራጨት ለድርድር የሚቀርቡ ባይሆንም፤ ለኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃን ቅድሚያ በመስጠት የህትመት መገናኛ ብዙኃንን ማግለሉ ተወግዶ ሁሉንም የመገናኛ ብዙኃን በእኩል ዓይን ማየት፣ መረጃ ለመስጠትና ሁነቶች ላይ ጋዜጠኞች እንዳይገኙ በመከልከል ለዘገባ ዝግ ማድረግ አሁን የተገኘውን የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ያጎናፀፈ ዘገባ ወደ ቀደመው የመረጃ እጦትና የአሉባልታ ዘገባ የሚመልስ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አሕመድ የአገር መሪነቱን ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ ሌብነት የአገር ጠላት መሆኑን፤ ከአገርና ከወገን ላይ መስረቅ አሳፋሪ እንደሆነ፣ በአገሪቱ ሠላም፣ ፍቅር፣ መረዳዳትና መተሳሰብ ካለ ልማታችን እንደሚጎለብትና ማደግ እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡

ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችለው ግን በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉት መገናኛ ብዙኃን አድልዎ ሳይደረግባቸውና መረጃ ሳይነፈጉ ሥራቸውን ማከናወን ሲችሉ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉንም መገናኛ ብዙኃን በእኩል ዓይን ማየትና ለመረጃ ግልፅ መሆን በይደር ወደ ጎን የሚተዉ ጉዳዮች ሊሆኑ አይገባም፡፡ ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ሰላም የጎላ ፋየዳ እንዳለው እሙን ነው፡፡

በአገሪቱ ነጻ ሚዲያ ከተስፋፋ፡  ሁሉም ህዝቦች በነጻነትና በእኩልነት የሚኖሩበት ሁንታ እውን ከሆነ፡ ካሁን በፊት ለጠፉ ጥፋቶች የቅር መባባል ከተቻለ፡ ይቅርታን ተከትሉ ሁሉም በመደመር አንድነቱን ማጠናከር ከቻለ አገራችን የማትለወጥበት ሁኔታ አየኖርም፡፡ አገሪቱ መለወጥ ከቻለች ደግሞ የህዝቧ ኑሮ መሻሻል እውን ይሆናል፡፡ ይህ ሲሳካ ከህብረተሰቡ ተጠቃሚነት የረጋገጣል፡፤ በመሆኑም ለውጡ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች በርካታ ፋየዳዎች ያሉት በመሆኑ ሁሉም ሕብረተሰብ ለስክታማነቱ ሊረባ,ረብ ይገባል፡፡