6ኛው የፋን ኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ በኮንሶ ተካሄደ

መጋቢት 10/2014 (ዋልታ) “ኑ ለኮንሶ እድገት እንሩጥ” በሚል መሪ ሃሳብ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ የ8 ኪሎ ሜትር ርቀት የፋን ኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ፡፡

በውድድሩ በሁለቱም ጾታ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ አትሌቶች የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ የፋን ኢትዮጵያ መሥራችና ባለቤት አትሌት ፋንቱ ሜጌሶ እና የውድድሩ ተባባሪ አዘጋጅ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳዊት ገበየሁ ተገኝተዋል።

ደግነት  መኩሪያ (ከኮንሶ ዞን)