ህልምን ወደ ፊልም የሚቀይረው መሳሪያ

#ቴክኖ_ቅምሻ

ጃፓን ሰዎች እንደገና እንዲያስታውሱ እና ህልማቸውን እንደ ፊልም እንዲመለከቱ የሚያስችል ልዩ መሣሪያ ሰርታለች።

በጃፓን ኪዮቶ የሚገኘው የኤ ቲ አር (ATR) ኮምፒውቲሽናል ኒውሮሳይንስ ላቦራቶሪ ተመራማሪዎች ህልምን የሚመዘግብ እና መልሶ የሚያጫወት እጅግ አስደናቂ መሳሪያ ሰርተዋል።

በዩኪያሱ ካሚታኒ (ዶ/ር) የሚመራው የተመራማሪዎች ቡድን ኤፍ ኤም አር አይ (FMRI) የአንጎል ስካን እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመጠቀም መሳሪያውን ሰርተዋል።

በተደረገ ሙከራ ያለሙትን ህልም ይዘት ሳይቀይር በመተንበይ ከ70 በመቶ በላይ ትክክለኛ ሆኖ መገኘቱን ፎሲ ቢት ዘግቧል።

ይህ ቴክኖሎጂ ስለ ንቃተ ህሊና ተፈጥሯዊ ግንዛቤዎችን በመስጠት እና የአእምሮ ጤና ምርመራዎችን በማገዝ ለኒውሮሳይንስ ብዙ ጥቅም ከመስጠቱ በተጨማሪ ሌሎች እምቅ ችሎታም አለው ተብሏል።

በህልም ትንተና ስሜቶችን እና የስነ-ልቦና ሁኔታዎችን በመረዳት ወደፊት በኒውሮሳይንስ ላይ ጥሩ እድገቶችን እንደሚያሳይ ታምኖበታል።

በየኔወርቅ መኮንን