ሊዮኔል ሜሲ ለ7ኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ

ኅዳር 21/2014 (ዋልታ) የአርጀንቲና እና የፓሪሴን ጀርሜን የፊት መስመር ተሰላፊ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ሜሲ ለ7ኛ ጊዜ የአለም ምርጡ ተጫዋች በመባል ተመርጧል፡፡

የ34 አመቱ ተጫዋች የሃገሩን ብሔራዊ ቡድን በአምበልነት እመራ ለኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ድል ያበቃ ሲሆን በውድድር አመቱ በአጠቃላይ 40 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

የዘንድሮው ባሎንዶር አሸናፊነትን ግምት ያገኘው ፖላንዳዊው የባየር ሙኒክ የፊት መስመር ተሰላፊ ሮበርት ሎዋንዶዊስኪ በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ፤ ጣሊናዊው የቼልሲ አማካይ ጆርጊኒሆ በ3ኛነት እንዲሁም ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተሰላፊ ካሪም ቤንዘማ በአራተኝነት አጠናቋል፡፡