መስከረም 30/2017 (አዲስ ዋልታ) 22 ጊዜ የግራንድ ስላም ውድድር ሻምፒዮን መሆን የቻለው ራፋኤል ናዳል በዚህ ከመጪው ሕዳር ውድድር በኋላ ከሜዳ ቴኒስ ጨዋታ ራሱን እንደሚያገል አስታወቀ።
የ38 ዓመቱ ተጫዋች በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው የዴቪስ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔንን በመወከል ይሳተፋል።
ሕዳር ላይ ከሚደረገው ከዚህ ውድድር በኋላም የቴኒስ ጨዋታ እንደሚያቆም ተናግሯል።
በፈረንጆቹ 2023 አብዛኛውን ጊዜ በጉዳት ካሳለፈ በኋላ ይሄኛው ዓመት የመጨረሻ የውድድር ዘመኑ እንደሚሆን አስታውቆ ነበር፡፡
ራፋኤል ናዳል 14 የፈረንሳይ ኦፕን፣ 4 የአሜሪካ ኦፕን፣ 2 የአውስትራሊያ ኦፕን እና ሌሎችንም የሜዳ ቴኒስ ውድድሮች በማሸነፍ በተደጋጋሚ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ተጫዋች መሆኑን ስካይ ስፖርት ዘግቧል።