በለንደን ማራቶን አትሌት ሲሳይ ለማ አሸነፈ

መስከረም 23/2014 (ዋልታ) ዛሬ በተካሄደው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች አመርቂ ዉጤት አስመዝግበዋል።
በወንዶች በተካሄደው ውድድር ሲሳይ ለማ 2:04.28 በሆነ ሰዓት ኬንያዊውን ቪንሰንት ኪፕቹምባን በማስከተል ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ፤ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሞስነት ገረመው ውድድሩን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።
ኢትዮጵያን አትሌቶች በለንደን ማራቶን በተከታታይ ዓመት በማሸነፍ አዲስ ታሪክም መፃፍ ችለዋል።
ሲሳይ ለማ አምና በተካሄደው የለንደን ማራቶን ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኬንያዊቷ ጄፕኮስጊ ስታሸነፍ ኢትዮጵያዊኖቹ ደጊቱ አዝመራው እና እሸቴ ቤክሪ ተከታትለው ገብተዋል።