አሜሪካ የሞደርና ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች

የኮቪድ-19 ክትባት የላብራቶሪ ሙከራ

አሜሪካ ሞደርና ሰራሹ የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ሰጠች።

ከሳምንት በፊት የአሜሪካ የምግብ እና መድሃኒት ተቆጣጣሪ የፋይዘር ባዮንቴክ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ መስጠቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የሞደርና ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ያገኘ ሁለተኛው ክትባት ሆኗል።

ባለስልጣናቱ 200 ሚሊዮን የሞደርና ክትባትን ለመግዛት ከስምምነት የደረሱ ሲሆን ከዚህም  ስድስት ሚሊየን የሚሆነው ለስርጭት ዝግጁ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አሜሪካ በቫይረሱ ክፉኛ ጉዳት ደረሰባት አገር ስትሆን እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አሃዝ 313 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ17 ነጥብ 5 ሚሊየን ሕዝብ በላይ ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።