አፄዎቹ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋገጡ

ሚያዝያ 28/2013 (ዋልታ) – የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መሪ የሆኑት ፋሲል ከነማዎች ተከታያቸው ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር አቻ መውጣታቸውን ተከትሎ ከወዲሁ በሂሳባዊ ስሌት ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ፋሲል ከነማ በቀጣይ ሳምንት ከድሬደዋ ከተማ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ዋንጫውን በይፋ ይረከባሉ።
(በሀብታሙ ገደቤ)