ነሐሴ 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ከ21 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ በባሎንዶር ሽልማት እጩ ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀሩ፡፡
ሽልማቱን አምስት ጊዜ ያሸነፈው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሮናልዶ ባለፈው ዓመትም የእጩነት እድል ሳያገኝ መቅረቱ ይታወሳል፡፡
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በበኩሉ 18 ጊዜ ታጭቶ ስምንተ ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን ዘንድሮ የአርጀንቲና ኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ቢያሸንፍም ለባሎንዶር እጩነት ግን ሳይሳካለት ቀርቷል።
የአውሮፓ ሊግ 2024 አሸናፊ የሆነችው ስፔን የ17 ዓመቱ የባርሴሎና የክንፍ ተጫዋች ላሚን ያማልን ጨምሮ 6 ተጫዋቾቿ በእጩ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡
ከሪያል ማድሪድ ጋር የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያነሱት ኒኮ ዊሊያምስ፣ አሌሃንድሮ ግሪማልዶ፣ ዳኒ ኦልሞ፣ ሮድሪ እና ዳኒ ካርቫጃል ለባሎንዶር 2024 እጩ ከሆኑት መካከል ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም እንግሊዝ ለኢሮ 2024 የፍፃሜ ውድድር እንድታልፍ የረዱ 6 ተጫዋቾች በ2024 የባሎንዶር እጩ 30 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ።