ግንቦት 15/2015 (ዋልታ) ዋትስአፕ የተሰኘው መልዕክት መላላኪያ ድር ተጠቃሚዎች መልዕክታቸውን ከላኩ በኋላ አርትዖት ማድረግ እንዲችሉ ሊፈቅድ ነው።
የዋትስአፕ ተፎካካሪ የሚባሉት ቴሌግራምና ሲግናል ለተጠቃሚዎች ይህን ይፈቅዳሉ ነው የተባለው።
ኩባንያው እንዳለው መልዕክት ከተላከ በኋላ እስከ 15 ደቂቃ ባለው ጊዜ ‘ኤዲት’ ሊደረግ ይችላል።
ዋትስአፕ የግዙፉ አሜሪካዊ ድርጅት ሜታ አካል ሲሆን ፌስቡክ እና ኢንስታግራምም እንዲሁ የሜታ ቤተሰብ ናቸው።
አዲሱ ቴክኖሎጂ ለ2 ቢሊዮን የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይፋ ይሆናል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።