አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 4ኛው ዓለም አቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎች ኮንፈረንስ ከ9ኛው የኢትዮ ኸልዝ ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን እየተካሄደ ይገኛል፡፡
“ለጋራ ርዕይ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ትብብርን በማጎልበት ጠንካራ አጋርነት መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ኮንፍረንሱ ላይ ከ100 በላይ ዓለምአቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎች በአካልና በበይነመረብ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ኮንፈረንሱ በሀገር ውስጥ የተመዘገበ በቂ አቅራቢ የሌላቸውን መድሃኒቶች አስተማማኝ አቅራቢ እንዲኖራቸው ከማስቻል ባለፈ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ለመሳብ ወሳኝ ነው ተብሏል።
በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ በመድሃኒትና የህክምና መገልገያ ምርቶች ላይ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የአልትራሳውንድ መሳሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተገጣጠመ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
በርካታ ህይወት አድን መድሃኒቶች አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየተመረቱ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በዚህም የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ከማርካት አንፃር ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል ተብሏል።
በዓለምሰገድ አሳዬ