የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደረሱ

ሚያዝያ 7/2014 (ዋልታ) በዓለም የምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ 50 ተሽከርካሪዎች መቐለ ደረሱ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው 50 ዕርዳታ የጫኑና የነዳጅ ቦቴ ተሽከርካሪዎች በሰላም መቐለ ደርሰዋል።
ተሽከርካሪወቹ 47 ምግብ፣ ዓልሚ ምግቦችን እና ሌሎች ሕይወት አድን ቁሳቁስ የጫኑ ሲሆኑ 3 ነዳጅ የጫኑ መሆናቸው ተገልጿል።
ከዚህ ውስጥ 1 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና የተለያየ ጥራጥሬ ሲሆን 700 ሜትሪክ ቶኑ ደግሞ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ የጤና የንጽህና መጠበቂያዎች እንደሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም 115 ሺሕ ሊትር ነዳጅም ከሰብአዊ እርዳታው ጋር መቐለ መድረሳቸው ተጠቁሟል።