የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንዲቀጥል ተወሰነ

መጋቢት 27/2014 (ዋልታ) የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚያዚያ ወር በነበረበት እንዲቀጥል የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

መንግሥት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ለማስቻል በሚያዚያ ወር/2014 ዓ.ም የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር/2014 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ ያለምንም ለውጥ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን ሚኒስቴሩ ለዋልታ በላከው መረጃ አመልክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!