የታንዛኒያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር የደረሰ የመጨረሻው ልዑክ ሆኗል

የታንዛኒያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የታንዛኒያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባህር ዳር የደረሰ የመጨረሻው የልዑክ ቡድን ሆኗል።

ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ማለዳ ባህር ዳር በመግባት በተፈሪ መኮንን ሆቴል ያረፈ ሲሆን፣ የኮቪድ-19 ምርመራም አድርጓል።

በምድብ ሀ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር 10 ሰዓት ላይ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡