የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ላይ የተደረገው ሙከራ ክትባቱ አስተማማኝ መሆኑን አመለከተ

መጋቢት 13 /2013 (ዋልታ) – የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ላይ በአሜሪካ፣ በቺሊና በፔሩ በተደረገ ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት የሌለውና አስተማማኝ መሆኑን የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በሶስቱ አገሮች በሁሉም የእድሜ ክልል በሚገኙ 32 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ላይ ባደረገው ምርምር ክትባቱ ውጤታማና ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑን ማረጋገጡን የሮይተርስን ዋቢ አድርጓ ኢዜአ ዘገቧል ፡፡