አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል በስዊዘርላንድ ናዮን ይፋ ተደርጓል።
በዚህ መሰረትም አርሰናል ከኔዘርላንድሱ ፒ ኤስ ቪ አይንድሆቨን እንዲሁም ሊቨርፑል ከፒ ኤስ ጂ ጋር ተደልድለዋል።
በተጨማሪም ባየርን ሙኒክ ከባየር ሊቨርኩሰን፣ ክለብ ብሩገ ከአስቶንቪላ፣ ቦሩሺያ ዶርትመንድ ከሊል፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ፣ ፌይኖርድ ከኢንተር ሚላን እና ቤኔፊካ ከባርሴሎና መደልደላቸውን የሊጉ መረጃ ያመላክታል፡፡
የጥሎ ማለፉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች የፊታችን የካቲት 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄዱ ይሆናል፡፡