ሚያዝያ 18/2013 (ዋልታ) – ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
በአፍሪካ ቮሊቦል ኮንፌዴሬሽን (ሲኤቪቢ) አስተናጋጅነት 32ኛው የአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር ከሚያዚያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በቱኒዚያ በመካሄድ ላይ ነው።
በውድድሩ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሁለቱም የኢትዮጵያ ቮሊቦል ክለቦች በውድድሩ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
በምድብ ሁለት የሚገኘው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአራት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የቡርኪናፋሶውን ኤስ ዱዋኔስ 3 ለ 1 አሸንፏል።
የአፍሪካ ቮሊቦል ኮንፌዴሬሽንን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በመጀመሪያ ተሳትፎ የመጀመሪያ ድሉን በማስመገብ ኢትዮጵያን እንዳኮራ ተገልጿል።
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ በምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታውን ዛሬ ከኮትዲቯሩ አሴክ ሚሞሳስ ጋር የሚያደርግ ሲሆን፣ ክለቡ በምድቡ ያደረጋቸውን የመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎች መሸነፉ ይታወሳል።
በሌላ በኩል በምድብ አንድ የሚገኘው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና የቡሩንዲው ሙዚንጋ ጨዋታቸውን ማድረግ ስኖርባቸው የሙዚንጋ ክለብ ተጫዋቾች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭነት ምክንያት ጨዋታውን ማድረግ እንደማይችሉ በመረጋገጡ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በፎርፌ ማሸነፉን ኮንፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት በምድቡ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በቱኒዚያዎቹ ሲኤስ ሰፋክሲያንና ኬሊቢያ ክለቦች መሸነፉ የሚታወስ ነው።
ክለቡ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከኬንያው ኬንያ ፕሪዝንስ ጋር ያደርጋል።
የአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለብ ውድድር እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይቆያልም ነው የተባለው።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/%D8%AA%D9%84%D9%81%D8%B2%D9%8A%D9%88%D9%86-%D9%88%D8%A7%D9%84%D8%AA%D8%A7-%D8%A8%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B1%D8%A8%D9%8A-Walta-TV-Arabic-102134881551994/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!