የኢትዮጵያ ፖራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) – በቶኪዮ 2020 ፖራሊምፒክ ጨዋታ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደገለት፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ በ3 አትሌቶች የተወከለ ሲሆን 1 ወርቅ ሜዳሊያ እና 2 ዲፕሎማ በማግኘት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ነው ውድድሩን ያጠናቀቀው፡፡
ቡድኑ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በሥነ ስርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሀብታሙ ሲሳይ እና የስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ማኅበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡