የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ ለማጥናት አስር ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችን የያዘ ቡድን በሚቀጥለው ወር ወደ ቻይና ዉሃን እንደሚያቀና የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ምርምሩን የሚያካሂደው ለወቀሳ ሳይሆን ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን ለመከላከል እንደሆነ ለአሶሽየትድ ፕረስ ተናግረዋል።
ለወረርሽኙ ጥፋተኛ የሆነውን አገር ለመፈለግ ሳይሆን፣ ምን እንደተከሰተ ለመረዳት መሞከር እና በእነዚያ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ወደፊት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንደሚቻል ለማየት እደሆነ ተገልጿል፡፡
የምርምሩ ዋና ዓላማ ቫይረሱ መቼ መዛመት እንደጀመረ እና መነሻው ዉሃን ይሁን አይሁን ለማወቅ እዲቻል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
ምርምሩ ከአራት እስከ አምስት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ አስነብቧል።