ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር የሴቶች 10 ሺሕ ሜትር አሸናፊ ሆነች

ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር

መጋቢት 20/2014 (ዋልታ) በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር የሴቶች 10 ሺሕ ሜትር አሸናፊ ሆነች፡፡

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ባለውና 2ኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺሕ ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ዉድድር የተከናወነ ሲሆን የኢትዮ ኤሌክትሪክ አትሌት የሆነችው ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር የሴቶች 10 ሺሕ ሜትር አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡

ሀዊ ፈይሳ ከመከላከያ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ አበራሽ ምንሰዋ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

በሌላ በኩል 800 ሜትር የሴቶች ውድድር አትሌት ወርቅነሽ መለሰ ከሲዳማ ቡና 1ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

አትሌት ወርቅነሽ መለሰ

በቀጣይ የ100 እና 800 ሜትር ፍፃሜ በሁለቱም ፆታ እና የ3 ሺሕ ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ወድድሮች ይደረጋሉ፡፡

ትላንት በተካሄደው የወንዶች 1 ሺሕ ሜትር ፍፃሜ ታደሰ ወርቁ ከደቡብ ፖሊስ አኛ፣ ሚልኬሳ መንገሻ ከኦሮሚያ ክልል 2ኛ እና ገመቹ ዲዳ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክለብ 3ኛ በመሆን ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡

ሀብታሙ ገደቤ (ከሀዋሳ)

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!