ፊፋ የዓለም ዋንጫን በየ2 ዓመቱ የማድረግ ውጥኔን ለመሰረዝ ፍቃደኛ ነኝ አለ

ጥቅምት 11/2014 (ዋልታ) ተቃውሞ የበዛበት ፊፋ የዓለም ዋንጫን በየ2 ዓመቱ የማድረግ ውጥኔን ለመሰረዝ ፍቃደኛ ነኝ አለ፡፡
የዓለም ዐቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ ከአውሮፓ እግር ኳስ መሪዎች ጋር በዝግ ከመከሩ በኋላ በሰጡት መግለጫ ዓለም ጀካልተቀበለው እቅዱ ውድቅ ደረጋል ብለዋል፡፡
የእግር ኳስ ማኅበሩ በየ4 ዓመቱ የሚደረገውን ውድድር ጊዜ ወደ 2 ዓመት ዝቅ ለማድረግ ያቀረበው እቅድ ከተለያዩ የእግር ኳስ ማኅራት፣ ቡድኖችና፣ ተጨዋቾችና አሰልጣኞች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
በእቅዱ ላይ ‹‹ውስን በሳል እና በርካታ ጉጉና ደስተኛ የሆኑ አስተያየቶችን እየሰማሁ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ በየክፍለ ዓለሙ ያለው ፍላጎት የተለያየ ነው፤ የእኔ ዓላማ ወደ አንድ ማምጣት ነው መምጣትም አለብን›› ብለዋል፡፡
የሆነው ሆኖ የጋራ መግባባት ካልተደረሰበት እቅዱ ውድቅ እንደሚደረግ ዓለም ማወቅ አለበት ሲሉም የተነሳው ተቃውሞ እንዲበርድ መጠየቃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
‹‹ለ100 ዓመት ባለበት የቀጠለን ነገር ልቀይር ስትል የተቀባይነቱ ጉዳይ ፈታኝ እንደሚሆን እረዳለሁ›› ያሉት ኢንፋንቲኖ ‹‹ሰዎች እንዲረጋገጉና ምክንያታዊ እንዲሆኑ እጠይቃለሁ›› ብለዋል፡፡ በመጪው ታኅሣሥ 12 የጋራ ምክረ ሃሳብን የያዘ ሰነድ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡