በአቶ አዲሱ አረጋ የሚመራ ልዑክ በቦረና ዞን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያስመረቀ ነው

                                                           አቶ አዲሱ አረጋ

ግንቦት 29/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የማህበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪ በሆኑት በአቶ አዲሱ አረጋ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ያቀፈ ልዑክ በቦረና ዞን በ62 ሚሊዮን ብር በጀት የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶችን እያስመረቀ ነዉ።

ልዑኩ በትላንትናው ዕለት በያቤሎ ከተማ በ2 መቶ ሚሊዮን ብር በጀት በላይ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን በማስመረቅ የጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በኤልወዬ ወረዳ ሂዲ አሌ ቀበሌ የተሰራ ትምህርት ቤትን አስመርቋል።
በኤልወዬ ወረዳ የተሰራው ከቡሌ ጎላ ቀበሌ እስከ ሳሪቴ የገጠር ቀበሌ 25 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ፣በተጨማሪም የሰዉ እና የከብቶች የዉሃ ፕሮጀክትም ተመርቋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት እና የማሀበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ይህ አመት እና መጪዉ ጊዜ ለቦረና ህዝብ የብርሃን ጊዜ ነዉ ብለዋል። ለዚህ ማሳያ ደግሞ በምረቃ ላይ የሚገኙ 136 ፕሮጀክቶች ናቸዉ ብለዋል።
በቦረና ዞን የኤልወዬ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከዚህ በፊት ምንም የመሰረተ ልማት እንደሌላቸው ገልፀው አሁን ችግራቸው በመቀረፉ ደስታኞች መሆናቸውን ገልጿል።
(በሶሬቻ ቀበኔቻ)