የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ባለሙያዎች የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ

ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ባለሙያዎች የጋራ ምክር ቤት ለማቋቋም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ከማስታወቂያ ባለሙያዎች ጋር ምክክር ያደረገ ሲሆን፣ የጋራ ምክር ቤቱ እንዲቋቋም በአብላጫ ድምፅ ተወስኗል።

ሰባት የጋራ ምክር ቤቱ የስራ አመራር ኮሚቴዎችም በአባላት ተመርጠዋል።

የማስታወቂያ ባለሙያው ሳምሶን ማሞ የጋራ ምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጧል።

የጋራ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠው ሳምሶን ማሞ የማስታወቂያው ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለዘርፉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱን ዓመታዊ ስብሰባን የሚመሩ ሶስት የጉባኤ ሰብሳቢዎች መረጣም ተካሂዷል።

የማስታወቂያ ስራን ጥራት ለመመዘን የሚያስችል አሰራር መዘርጋት እና ሙያተኞችን ማብቃት ላይ ትኩረት በማድረግ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ይሰራልም ተብሏል።

(በትዕግስት ዘላለም)