በቅድመ ምርጫው የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተገለጸ

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በቅድመ ምርጫው ከፍተኛ ሚና  እንደነበራቸው ተገለጸ፡፡

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ ድልድልን በተመለከተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህም 46 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 143 የግል ተወዳዳሪዎች በ57 መገናኛ ብዙሃን ፖሊሲዎቻቸውን ማስተዋወቅ መቻላቸው ተገልጿል፡፡

በሬዲዮ 838፣ በቴሌቪዥን ደግሞ 576 ሰዓታትን መጠቀም ሲቻል 810 የጋዜጣ አምዶችም ለነጻ አየር ሰዓት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

(በሰለሞን በየነ)