የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ጽህፈት ቤቱ ከዚህ ቀደም የሚያደርገውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በመቀጠል የቦርሳ እና ጫማ ስጦታዎችን ባስገነባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና በአካባቢው ለሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በስጦታ ማበርከቱን ገልጿል።

የቁሳቁስ ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ጦሳ ፈላና፣ ደባርቅ፣ ማሻ ወረዳ እና አጋሮ እንደሚገኙ ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።