በጅማ ዞን በሸሻ ከተማ መራጮች ድምጽ እየሰጡ ነው

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በጅማ ዞን ጐማ ወረዳ በሻሻ ከተማ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በመውጣት እየመረጠ ይገኛል፡፡
በበሻሻ ከተማ ሀሮ እና ሰኮቴ የተሰኙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፣ በሀሮ የምርጫ ጣቢያ 1500 መራጮች በሰኮቴ 789 መራጮች ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
(በሜሮን መስፍን)