በቢሾፍቱ ከተማ በግማሽ ቀን ውስጥ 44 ሺህ 641 መራጮች ድምፅ መስጠታቸው ተገለጸ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የአድአ እንድ ምርጫ ክልል ሀላፊ አቶ መሰረት አበበ እንዳሉት በከተማዋ ባሉ 113 የምርጫ ጣቢያዎች 44 ሺህ 641 ዜጎች ድምፅ ሰጥተዋል።

ከመራጮቹ መካከል ወንድ 22 ሺህ 22 ሲሆን፣ ሴት 22 ሺህ 619 በአጠቃላይ 44 ሺህ 641 መሆናቸው ተጠቁሟል።

565 የምርጫ አስፈፃሚዎች በምርጫው የተሳተፉ ሲሆን፣ 226 የተፎካካሪ ፓርቲዎች ተወካዮች እንደሚገኙ የተነገረ ቢሆንም፤ የተገኙት ግን የብልፅግና ፓርቲ ተወካዮች ብቻ ናቸው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረትም ምርጫውን ታዝቧል ነው ያሉት።

(በትዕግስት ዘላለም)