በዳውሮ ዞን፣ ወላይታ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው

ሰኔ 15/2013 (ዋልታ) – በዳውሮ ዞን፣ ወላይታ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ ይገኛል።

በወላይታ ዞን ሁምቦ ጠበላ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ተገልጸው፣ ህብረተሰቡም ጊዜያዊ ውጤቶችን እየተመለከተ እንደሚገኝ ደሬቴድ ዘግቧል።

በየም ልዩ ወረዳ በሳጃ ከተማ ከማለዳው ጀምሮ ጊዜያዊ ውጤት በተለጠፈባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች ውጤቱን እየተመለከቱ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም በዳውሮ ዞን በሚገኙ  የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምጽ ውጤት ይፋ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዞኑ የሚወዳደሩ አራት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎችም በዘንድሮ ምርጫ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤቱን በፀጋ እንዲቀበሉ ጥሪ አቅበዋል፡፡