ሴቶችን ለመሪነት ማብቃት ለሀገር ዕድገትና ልማት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 16/2013(ዋልታ) – ሴቶችን ለመሪነት ማብቃት ለሀገር ዕድገትና ልማት ፋይዳ እንዳለው የኢፌዲሬ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዝደንቷ ‘‘ውመን ፖለቲካል ሊደርስ’’ የተባለ ድርጅት ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሀፊ ጋር በመሆን ባዘጋጀዉ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ ሴቶችን ይበልጥ ወደ አመራር ለማምጣት ያግዛሉ ብለዉ ያሏቸዉን የመፍትሄ ሀሳቦች ማንሳታቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሴቶችን በአመራር ክህሎት ማሰልጠን፣ በመሪነት ቦታ ላይ ያሉ ሴቶች ለሌሎች የምክርና የስልጠና ድጋፍ መስጠት፣ ሴቶች እርስ በራሳቸዉ የመደጋገፍና አብሮ የመስራት ባህልን ማዳበር እንዲሁም እድሉ ከተሰጣቸዉ ሴቶች ሰርተዉ ማሳየት እንደሚችሉ ማመን ይገኙበታል፡፡

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ በኢትዮጵያ ሴቶችን ለአመራር ከማብቃት አኳያ በተለያዩ ደረጃዎች እየተተገበሩ ያሉ መርሀ ግብሮች ማስጀመው ይታወሳል፡፡