ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ነገ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ አሳሰቡ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ነገ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ አሳሰቡ፡፡

 

ባለፈው ሳምንት ለ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሰኞ በሚዘጉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ምትክ ይህ ቅዳሜ የሥራ ቀን እንደሚሆን አሳውቀን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስለሆነም ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ነገ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስባለሁ” ብለዋል፡፡