ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጣ የጋዜጠኞች ቡድን በኬንያ የላሙ ወደብን እየጎበኘ ነው

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – ከኢትዮጵያ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙኃን የተውጣጣ የጋዜጠኞች ቡድን በኬንያ የላሙ ወደብ ጉብኝት ጀምሯል።

የላሙ ክልል ምክትል ገዢ አብዱል ከሪም ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን በሁለት ሀገር የሚኖሩ አንድ ዜጎች ናቸው ብለዋል፡፡

አክለውም የላሙ ወደብ ግንባታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ያጠናክረዋል ማለታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።