ኢሶዴፓ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ ሰጥቷል

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፓርቲው በዋናነት በተወዳደረባቸው የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደጋፊዎቹ በአግባቡ  እንዳይመርጡ አስቸጋሪ የሆኑ ከ10 በላይ ከፍተኛ ችግሮች እንደገጠመው ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ውጤቱን ይፋ የማድረግ ሂደት ከምርጫ ቦርድ ትክክለኛና አሳማኝ ለጥያቄያችን መልስ እንደሚሰጠን ትልቅ ተስፋ አለን ያለው ፓርቲው ውጤቱን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል፡፡

በመግለጫውም ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ስርአት የተላበሰ የተባለው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)