የጀነራል ሰዓረ መኮንንና የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት በቅርቡ ይመረቃል

የጀነራል ሰዓረ መኮንን ሀውልት

ሰኔ 21/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞው የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት በቅርቡ እንደሚመረቅ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ ጥላሁን ወርቁ ሀውልቱ ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በቅርቡ የጀነራሉ እና የአርቲስቱ ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶች እና ጓደኞች በተገኙበት የሚመረቅ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት የተሰራው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለ የስነ ጥበብ እና የዲዛይን ትምህርት ቤት ሲሆን፣ የጀነራል ሰዓረ መኮንን ደግሞ በአርቲስት ተስፋዬ ገብሬ መሠራቱን የከተማ አስተዳደሩ የኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሀይለማርያም ገልጸዋል።

(በሜሮን መስፍን)