የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የችግኝ ተከላ መርኃግብር አካሄዱ

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በለገዳዲ የውሃ ማጣሪያ ግድብ ዙሪያ ከ10 ሺህ በላይ ችግኞች ተክለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ከሆኑ ሰባት ተቋማት የተውጣጡ ከ500 በላይ ሰራቸኞች እና የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በግድቡ አካባቢ የተተከሉት ችግኞች የአካባቢውን ስነ ምህዳር የሚጠብቁ፤ ለምግብነትም የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አክለውም በሌሎች አካባቢዎችም የመትከሉ ስራ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ለዘንድሮው መርሃግብር ሚኒስቴሩ ከ94 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ ማዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

(በተስፋዬ አባተ)