ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኞች የመልካም እድል ምኞታቸውን ገለጹ

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የመልካም እድል ምኞት መልዕከት አስተላለፉ፡፡

የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች በይፋ ተጀምሯል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ “ዛሬ በመዲናችን ከ 76 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ 174 የመፈተኛ ጣቢያዎች የ 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በመዉሰድ ላይ ይገኛሉ ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ዉጤት እንዲገጥማችው በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ” ብለዋል።

በተያየዘ የክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እየተሰጠ ሲሆን ከዛሬ እስከ ሰኔ 25፣2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡