ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 386 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – ከሳዑዲ አረቢያ በትናትናው ዕለት 2 ሺህ 386 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።