ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 351 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 351 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን  ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም በትናትናው ዕለት 2 ሺህ 351 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡