ሰኔ 29/2013 (ዋልታ) – የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 3ሺህ 200 የሚሆኑ በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡
ለአዲስ ገቢ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር አህመድ ሙስጠፋ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕትክት ያስተላለፉ ሲሆን ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ማተኮር እንዳለባቸው አሳበዋል፡፡
አክለውም ለመላው የሚዛን አማን ከተማና የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ለተማሪዎቹ ስላደረገው አቀባበል አመስግነዋል፡፡
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮ የሚቀበላቸውን ተማሪዎቹን ባሉት ሶስት ጊቢዎች ተቀብሎ የሚያስተምር ሲሆን እነዚህ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ባሉት ስድስት ኮሌጆች እና ሁለት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚገኙ ከ45 በላይ የትምህርት መስኮች ውስጥ የሚሰለጥኑ ናቸው፡፡
የቅበላ ጊዜውም ከሰኔ 29 እስከ 30 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
(በዮሴፍ ታደሰ)