ሃምሌ 03/2013 (ዋልታ) – 2 ሺህ 536 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቀ፡፡
በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 333 ሴቶችና 161 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 536 ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ አቀባበል ያደረገላቸው መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።