በህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚደርሰውን ጫና የሚያወግዝ ሰልፍ ሊካሄድ ነው


ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) –
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚደርሰውን ጫና የሚያወግዝ ሀገር አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡
ሰልፉ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ለህዳሴ ግድቡ ድጋፍ እና የውጭ አገራት ጫናን መቃወሚያ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ዩዝ ኔትወርክ ፎር ሰስቴይነብል ዴቨሎፕመንት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤትና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጋር ባዘጋጁት ሰልፍ ከ5 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)