ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – ኢትዮ ቴሌኮም በ2013 በጀት አመት 56 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የበጀት አመቱን ስራ አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ተቋሙ ከእቅዱ በላይ 101 ነጥብ 7 በመቶ አፈፃፀም እንዳስመዘገ ገልጸዋል፡፡
ገቢው ከባለፈው አመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀርም 18 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተናግረዋል።
ከደበኞች ብዝት አንፃርም አሁን ላይ ተቋሙ በስራው ማሻሻያ 56 ነጥብ 2 ሚሊየን ደንበኞችን ማፍራት ተችሏል ነው የተባለው።
ይህም ከባለፈው አመት ቁጥር አንፃር በ22 በመቶ እድገት ማሳየቱን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጠቁመዋል፡፡
ከ2010 ጀምሮ በተቋሙ በተሰራው ሪፎርም በትርፍም በደንበኞች ብዛትም ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡ ነው በማብራሪያው የተጠቀሰው።
የደንበኛች ቁጥር በ2010 ከነበረበት 37 ነጥብ 9 ሚሊየን አሁን ላይ 56.2 ሚሊየን እደደረሰ በመረጃው ተመላክቷል።
(በደምሰው በነበሩ)