306 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ሐምሌ 10/2013 (ዋልታ) – በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት በትናንትናው ዕለት 306 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ አቀባበል ማድረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።