1442ኛው ኢደል አደሐ በዓል በአዳስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ነው

ሐምሌ 13/2013 (ዋልታ)- 1442ኛው ኢደል አደሐ (አረፋ) በዓል በደማቅ ሁኔታ በአዳስ አበባ ስታዲየም እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዓሉ የዒድ ሠላት ስግደትን ጨምር የተለያዩ የእምነቱ ስርዓቶች እየተከናወኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ እንዲሁም የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በበዓሉ ታዳሚ ሆነዋል፡፡

(በድልዓብ ለማና ሰለሞን በየነ)