የመዲናዋ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መደገፍ በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ እየተወያዩ ነው

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መደገፍ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መደገፍና ማገዝ በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

‘‘ክብር ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሠራዊት’’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተሳትፈዋል።

የውይይት መድረኩን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙና የሃገር መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች መርተውታል።

የውይይቱ ዓላማም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሃገር መከላከያ ሠራዊት እያደረጉ ያሉትን ሕዝባዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከር መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል።