የቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀመራል

የቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤት

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እንደገለጹት፣ ምክር ቤቱ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡

ጉባኤው የክልሉ ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2013 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል፡፡

እንዲሁም የክልሉን የ2014 በጀት ዓመት በጀት ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክትል አፈ-ጉባኤዋ ማሳወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡