አቶ አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባ ሰጡ

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባ ሰጡ።

የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ለአሚኮ እንዳስታወቀው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበዋል።

ሌሎች ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማትን እንዲመሩ በርዕሰ መሥተዳድሩ ምደባ ተሰጥቷል።